የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ2013ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛው መርሐግብር በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ የተለያዩ የስልጠና ዘርፎች አመልካቾችን ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመማር ፍላጐት ያላችሁና የትምህርት ሚኒስቴርን የመግቢያ መስፈርት ማሟላት የምትችሉ አመልካቾች ከመስከረም 13 – 26/2013ዓ.ም ድረስ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽ የተለቀቀውን የመመዝገቢያ ቅጽ ካላችሁበት ሆናችሁ በመሙላት አልያም በዩኒቨርስቲው ዋናው ሬጅስትራር ጽ/ቤት (ዋናው ካምፓስ) በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያስታውቃል፡፡