የመምህራን ቅጥር ማስታወቂያ

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመምህር እጥረት ባለባቸው የትምህርት ክፍሎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸውንና ውጤታቸው ለወንድ ከ2.75 በላይ ለሴት ከ2.5 በላይ የሆኑትን ምሩቃን አወዳድሮ በረዳት ምሩቅ ደረጃ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በረዳት መምህርነት ለመቀጠር የምትፈልጉ አመልካቾች ከ22/10/2009 ዓ.ም ጀምሮ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አስተዳደር ቢሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሴት አመልካቾችን የምናበረታታ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መምህራን  የሚፈለግባቸው የትምህርት መስኮችና የሚፈለገው የመምህራን ብዛት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡  

  1. በአካውንቲንግ ትምህርት ክፍል ብዛት 05 (አምስት)
  2. በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ብዛት 04 (አራት)
  3. በሆስፒታሊቲና ቱሪዝም ማነጅመንት ትምህርት ክፍል  ብዛት 03 (ሶስት)
  4. በባንኪንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ብዛት 03 (ሶስት)

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ